በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር የስልጠና ማኑዋል

 

በዶሮ ዕርባታ ላይ የተዘጋጀ አጭር የስልጠና ማኑዋል

ዶሮ ማለት የአእዋፋት ዝርያ ሆነዉ ለሰዉ ልጅ ጥቅም የሚሰጡ(እንቁላል፤ስጋ) እና በሰዉ ልጅ ቁጥጥር ስር ያሉ ወይንም ለማዳ የአእዋፍ ዝርያ ማለት ነዉ፡፡ የዶሮ ዕርባታ ማለት ደግሞ ዶሮዎች እና የዶሮ ዉጤቶች የሚገኝበት ቦታ/ስፍራ ማለት ነዉ፡፡ የዶሮ አረባብ ዘዴን በሁለት መክፈል እንችላለን፡፡ እነሱም፡- በልምድ/ልቅ እና ዘመናዊ አረባብ ዘዴ ናቸዉ፡፡ በልምድ/ልቅ የዶሮ አረባብ ዘዴ ኋላቀር የአረባብ ዘዴ ስለ ሆነ ዉጤታማ አያደርግም፡፡ ዘመናዊ የዶሮ አረባብ ዘዴ ዶሮዎችን በዘመናዊ/በተሻለ መልክ ማርባት ማለት ነዉ፡፡ በዚህ አጭር የስልጠና ማኑዋል ዉስጥ ስለ ዘመናዊ የዶሮ አረባብ ዘዴን በሰፊዉ እንመለካታለን፡፡

Tags: