የዕንቁላል ጣይ ዝርያ ዶሮዎች የመኖ ቀመርና የተመጣጠነ ድብልቅ መኖ ዝግጅት ማንዋል

 

የዕንቁላል ጣይ ዝርያ ዶሮዎች የመኖ ቀመርና የተመጣጠነ ድብልቅ መኖ ዝግጅት ማንዋል

 

አገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ስላላትና ቁጥሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የምግብ ዋስትናን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል። የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ደግሞ ከሰብል ምርት ባልተናነሰ መልኩ በአነስተኛ መሬትና በመካከለኛ ወጪ ሊረቡ የሚችሉ እንስሳት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው። የዕንቁላል ዶሮ ዕርባታ ለመጀመር ከፍተኛ ወጪን ከማይጠይቁና ምርታቸውም በአነስተኛ ዋጋ ለጠተቃሚዎች መድረስ ከሚችሉ የእንስሳት ዕርባታ ዘርፎች አንዱ ነው። ዘመናዊ የእንቁላል ዕርባታ በተገቢው ሁኔታ የተከናወነ እንደሆነ ከፍተኛ የእንቁላል ምርት ከማስገኘቱም ባሻገር ምርት በሚያቆሙበት ወቅትም የአገራችን ተጠቃሚዎች የሚፈልጉት ዓይነት የዶሮ ሥጋ ይሰጣሉ።

Tags: